The Rising South

አእምሮአዊ ሉዓላዊነት፦ በአፍሪካ እውቀትን የሚቆጣጠረው ማን ነው?

Sputnik
"ራሴን እንደ ምሁር ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ተማሪ አድርጌ ባስቀመጥኩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በቋንቋዎቻችን ውስጥ ያለውን ጥልቅ የፍልስፍና ይዘት ይበልጥ ለመረዳት ችያለሁ።[…]ሰዎች ባሉበት ሁሉ አስተሳሰብ አለ፤ አስተሳሰብ ባለበት ሁሉ እውቀት አለ፤ እውቀት ባለበት ሁሉ ደግሞ ፍልስፍና አለ፡፡” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቭርስቲ /ዩኒሳ/ መምህርት ፕ/ር ሻባላኒ ኖኩቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በአእምሮአዊ ሉዓላዊነት እና የአፍሪካን ትምህርት ከቅኝ ግዛት ተጽዕኖ ነፃ ስለማውጣት በሚመለከት ከፕ/ር ሻባናኒ ኖኩቱላ ጋር አፍሪካ የፖለቲካ ነፃነት ብታገኝም፣ ብዙ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም የአፍሪካን ታሪክ፣ ቋንቋዎች እና የእውቀት ሥርዓቶች ወደ ጎን በሚገፉ የቅኝ ግዛት ዘመን መዋቅሮች ውስጥ እየሰሩ ስለሚገኙበት ምክንያት፣ እነዚህ ውርሶች እንዴት እንደቀጠሉ እና መቀየር ስለሚቻልባቸው መንገዶች እንወያያለን፡፡

“ምናልባትም የ21ኛው ክ/ዘመን 'መሃይም' ተብለው የሚጠሩት ማንበብና መጻፍ የማይችሉት ሳይሆኑ፤ የተሳሳቱ እውቀቶችን መተው እና አዳዲስ እውቀቶችን መልሶ መማር የማይችሉት ናቸው።" በማለትም ፕሮፌሰር ሻባላኒ አክለዋል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox