''እያንዳንዱ የጤና ቴክኖሎጂ የራሱ ሳይንሳዊ የውጤታማነት መለኪያ አለው። ለአብነትም የመመርመሪያ መሣሪያዎችን መውሰድ እንችላለን —ሀገራችን ራሷን በክትባት አቅም ማብቃት ይኖርባታል፣ እኛም እንደተመራማሪ ክትባቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት አለብን '' ሲሉ በዘርፉ የረጅም ዓመታት ተመራማሪው ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በምርምር፣ አዲስ ሀሳብ በማፍለቅ እንዲሁም ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎችን በመተግበር በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና ተያያዥ ሀገር አቀፍ ችግሮችን መቅረፍ ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች በዘርፉ የረጅም ዓመታት ተመራማሪው ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው ጋር ዳሰናል። በክፍል ሁለት ደግሞ ታህሳስ 1፣ 2025 በመላው ዓለም የተከበረውን የኤች አይ ቪ ቀንን መነሻ በማድረግ የጤና አጠባበቅ ስርዓትና ተደራሽነትን በአቤት ሆስፒታል የድንገተኛና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ፀጋዬ ገብረ አናንያ ጋር ቃኝተነዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox