Sovereignty Sources

የኢትዮጵያ 2029 የአፍሪካ ዋንጫ ማሰናዳት ጥያቄ፦ ከእግርኳስ የሚሻገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶቹ

Sputnik

''ሀገራችን እንደ አፍሪካ ዋንጫ ያሉ ትልልቅ ውድድሮችን ማዘጋጀት ከቻለች የሚያስገኙላት በረከቶች በርካታ ናቸው - ኢትዮጵያ አንድ ወቅት እንደ ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ዓይነት ህይወቱን ለእግር ኳስ የሠጠ ታላቅ የአግር ኳስ መሪ የነበራት ሀገር ናት'' ሲል የስፖርት ጋዜጠኛው ዮናስ አዘዘ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።

ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችው ይፋዊ ጥያቄ በእግር ኳስ አውድ ከሚገለፁ ጥቅሞች ባሻገር የሚያስገኝላትን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያውና ሌሎች ተያያዥ ጥቅሞችን ከስፖርት ጋዜጠኛው ዮናስ አዘዘ ጋር ቃኝተነዋል። በሉዋንዳ አንጎላ የተካሄደውን 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎችን በተመለከተ በሥፍራው ተገኝቶ ከተከታተለው ሌላኛው የስፖርት ጋዜጠኛ ፉአድ ኢንድሪስ ጋር በክፍል ሁለት ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox