Sovereignty Sources

የናኖ ቴክኖሎጂ ትሩፋት፡ ለንጹህ የኃይል ምንጭና ቀጠናዊ ትስስር

Sputnik
''የፀሃይ ብርሃንን ተጠቅም የኃይል ምንጭን ለመፍጠር ናኖ ቴክኖሎጂ ጉልህ አስተዋፅዖ አለው። በተጨማሪም የካርበን ልቀትን ለመቆጣጠር የናኖ ቁሶች ጠቃሚ እንደመሆናቸው በሀገራችን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሚደረግ ትብብር በፕሮጀክት ጀረጃ እየተሰራበት ነው '' ሲሉ በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የነገን ዋስትና ለማረጋገጥ፣ ቀጠናዊ ትብብርና ለማሳደግ የጋራ ችግሮችን ለመቅረፍ ንፁህ ኢነርጂ እና አካባቢያዊ ከተበከለ ነገር ለማንጻት ናኖ ቴክኖሎጂ ስላለው ፋይዳ የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞን (ዶ/ር) በእንግድነት ጋብዘናቸዋል። የምርምር ግኝቶችን ወደ ገበያ በማውጣት የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ትግበራዎችን ማረጋገጥ እንዲሁም ከብሪክስ አባላት ጋር ትብብርን መፍጠርን በተመለከተ ከቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን ኮመርሻላይዜሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኡስማን ኡመርን ጋር የተደረገው ቆይታም ሌላኛው ጉዳያችን ነው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox