"የብሪክስ አገራት አንዱ ስምምነት በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በምርምር እና በፈጠራ፣ እንዲሁም በተለያዩ የፋርማሲዩቲካል እና የሕክምና መሣሪያዎች ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት ነው። ይህም ከስኳር እና ከሌሎች መሰል ልማዳዊ አሠራሮች ወደ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ተሳትፎ ለመሸጋገር ያስችላል። ምክንያቱም የብሪክስ መመሪያዎች፣ ስምምነቶች እና ፍላጎቶች ከነዚህ መሰል ልማዳዊ አሠራሮች ወደ ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች በመሸጋገር በእስያ እንዲሁም በአፍሪካ አገራት፣ በተለይም በኢትዮጵያ፣ ምርትን እና ምርታማነትን ማሳደግ ነው" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ከሆኑት መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር) ጋር ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ እራሷን እንዴት እያዘጋጀች እንደሆነ እና በተለይም የህንድ ሚና ላይ ትኩረት በማድረግ የተወያየን ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) የገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርቶች ስለመተካት በጥልቀት የሰጡት ትንታኔ በሁለተኛው ክፍል ተካትቷል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ :
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox