''በግብርናው ዘርፍ የበለጠ መሠራት ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የገበሬውን ችግሮች ለመቅረፍ በጥናትና ምርምር እንዲሁም ቴክኖሎጂዎች የተደገፉ ተግባራት መሠራት አለባቸው። ለዚህ በጋራ መሥራት ይቻላል፣ ልምዶችንም ማደበር ያስፈልጋል — የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በርስ አጋርነትና ሁለንተናዊ ትብብር መፍጠር ይኖርባቸዋል '' ሲሉ በጥናትና ምርምር ያሳለፉት፣ በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሙያቸው ያለገለገሉት አቶ ወርቅነህ አበበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል የአፍሪካ አህጉር የግብርና ዘርፍን በቴክኖሎጂ ሽግግር በመደገፍ ወደፊት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ለመወያየት በጥናትና ምርምር ያሳለፉት፣ በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሙያቸው ያለገለገሉት አቶ ወርቅነህ አበበን ጋብዘናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ለውይይት የአፍሪካ አህጉር ለረጅም ጊዜያት እየሰራችበት ያለችውን የደህነት ቅነሳ ሞዴሎች ይመለከታል፡፡ በዚህ ረገድ የተሻሻለ ልማትና ዕድገትን ለመፍጠር ሁነኛ መፍትሄ መፍጠር ይገባል የሚለውን የስርዓተ ትምህርትና የንጽጽር ፖሊሲ ጥናት ባለሙያው እንግዳችን እንዳለው ፉፋ ቁፊ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox