The Rising South

የበርሊን ኮንፈረንስ፡-የምዕራባውያን ኢ-ፍትሐዊነት እና በደል በአፍካውያን ላይ

Sputnik
“አፍሪካውያን ሸማቾች እንዲሆኑ፣ ከዛ በፊት አይተው የማያውቁትን የአውሮፓ እቃ መሸመት፣ መጠቀም እንዲችሉ ብዙ ተዘዋዋሪ መንገዶችን ይጠቀማሉ። አፍሪካውያን ያለነዛ ሽቀጦች ህይወታቸውን መምራት እንዳይችሉ አድርገው አጣብቂኝ ውስጥ ይከቷቸዋል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ደቻሳ አበበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የአውሮፓ ወራሪ ኃይሎች በበርሊን ኮንፈረንስ ላይ ያደረጉት አፍሪካን የመቀራመት ስምምነት በአፍሪካ እና አፍሪካውያን ላይ ስላንጸባረቁት ኢ-ፍትሐዊነት እና ስላደረሱት በደል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ከሆኑት ደቻሳ አበበ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እንዳስሳለን፡፡ የኢትዮጵያ የበቆሎ ምርት ያለበትን ደረጃ እና በቆሎ የሀገሪቱን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንጻር ስላለው ሚና በበቆሎ ሰብል ላይ ተመራማሪ ቢተው ጥላሁን (ዶ/ር) ጋር ያደረግነው ውይይትም በሁለተኛው ክፍል ይዳሰሳል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox