Sovereignty Sources

ከስትራተጂ እስከ ሉዓላዊነት የዘለቀው የአፍሪካ የሠው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ

Sputnik
''መሠረታዊው መልዕክት፣ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በአፍሪካዊያን ለአፍሪካዊያን መገንባት ይኖርበታል የሚል መሆን አለበት — ለአካባቢያው ችግሮችም በሀገር በቀል እውቀቶች ነው መፍትሔ መሠጠት ያለበት። ስለዚህ ሉዓላዊነት የውይይቱ ማዕከላዊ ነጥብ ይሆናል ማለት ነው'' ሲሉ በኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የሠው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያው ዮናስ ገብረሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በሁለት ዐበይት ሀሳቦች ዙሪያ በምንወያይበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ በመጀመሪያው ክፍል በአፍሪካ አህጉር ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን እያሳየ የመጣው የሠው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የበለጠ እንዲጎለብት ደግሞ ከስትራቴጂ ወደ ሉዓላዊነት ማሸጋገርን በተመለከተ በኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያው ዮናስ ገብረሚካኤል ጋር ተወያይተናል። ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ያላትን ቁልፍ ሚና በሚመለከት ከደቡብ አፍሪካ የግብርና ኢኒሼቲቭ ፕሬዝዳንት ቲዮ ደ ጃገር (ዶ/ር) ጋር ያደረገነው ውይይትም በሁለተኛው ክፍል የምንቃኘው የፕሮግራሙ አካል ነው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox