“በእኛ የሥነ ምግባር እሴቶች ላይ በመመሥረት፣ ለህብረተሰቦቻችንና ለኅብረተሰባችን ጥሩ የሆነውንና አስፈላጊ የሆነውን ነገር መከላከል አለብን። በትክክለኛ መረጃ እና በተገቢው ግንኙነት በትክክል መከላከል አለብን። […]የመንግሥት መዋቅር በሽማግሌዎች ላይ እምነት ሊኖረውና ሥልጣንን በአግባቡ መወከል አለበት፤ ዝም ብሎ በስም ብቻ ሳይሆን።” ሲሉ የኢትዮጵያ የሽማግሌዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ተስፋጽዮን ደለለው (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሦስት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ የሽማግሌዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር ተስፋጽዮን ደለለው (ዶ/ር) ጋር ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ሰላምን መገንባትና ማንነትን መጠበቅበተመለከተ ሚናቸውን እንቃኛለን፡፡ በሁለተኛውም ክፍል ደግሞ የፓን-አፍሪካ የክፍያ ሥርዓትና እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ስትራቴጂ ተስፋዎችን ለአፍሪካ የፋይናንስ ሉዓላዊነት ያላቸውን ሚና እንቃኛለን፡፡ በመጨረሻውም ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ በተገኙ ግንዛቤዎች የአፍሪካን የኃይል ተቃርኖ እንመረምራለን ለዚህም በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልገሎት የ 'ኤኤምአይና ስካዳ' ሥራ አስኪያጅ ከአቶ ዘሪሁን አበበ ጋር ባደረነው ውይይት ዳስሰነዋል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡