“ይህ ክስ ለመላው አህጉር ታላቅ ምሳሌ የሚሆን የሕግ መሠረት መጣል የቻለ ነው። […] በአኅጉራዊና ክልላዊ አካላት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባለሥልጣናት ውሳኔያቸው የማይነኩ እና የማይጠየቁ እንደሆኑ ሊያስቡ ይችላሉ። ነገር ግን መጠየቅ አለበት። እናም፣ በዚህ ዓይነት ክስ የሚጠቀሙት የመጀመሪያው አካል ክሱን ያቀረበው ግለሰብ ሳይሆን፣ ተቋሙ ራሱ ነው።” ሲሉ የፓን አፍሪካ ህግ ባለሙያዎች ህብረት (PALU) እና የኢትዮጵያ የጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ጌታቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የፓን አፍሪካ ህግ ባለሙያዎች ህብረት እና የኢትዮጵያ የጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት ከሆኑት ከአቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ጋር በመሆን በምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የፍትህ ፍርድ ቤት ያገኙትን ታሪካዊ ድል — በተመለከተ የተወያየን ሲሆን፤ የ2025 የአፍሪካ ሴት የመገናኛ ብዙኃን ዘጠነኛ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተን የሴቶችን ውክልና፣ በአፍሪካ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀና ሁሉን ያካተተ የሚዲያ ምህዳር መገንባትን በተመለከተ ከዶ/ር የሚሲ አኪንቦቦላ፣ ጆይ አዲግዌ እና ማሪያማ ባህ ጋር ያደረነው ቆይታ በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ተዳስሷል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox