The Rising South

የማካካሻ ፍትህ ፦ ለአፍሪካ ለምን አስፈላጊና ወሳኝ ጥያቄ ሆነ ?

Sputnik
“የቅኝ ግዛት ካሳ ጉዳይ ማንሳት ከታሪካዊ እይታ አንጻር ብቻ ሳይሆን ከፖለቲካዊና ከሥነ-ልቦናዊ እይታ አንጻርም ጭምር በጣም አስፈላጊ ነው። ይህም አሁን ያለው የምዕራቡ ዓለም ትውልድ እንዲሁም አሁን በአፍሪካ እና በሌሎች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የቅኝ ግዛት ሥር በነበሩ አገሮች የሚኖሩት ትውልዶች በእነዚህ አካባቢዎች ጭቆና፣ ብዝበዛ እና አሰቃቂ የቅኝ ግዛት አገዛዝ እንደነበረ ማወቅ አለባቸው።” ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ፣ የቅኝ ግዛት ካሳ ለአፍሪካ ክብር፣ ሉዓላዊነትና ልማት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት እንዲሁም በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ በናይጄሪያ ሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን የሕግ እና ክስ ጉዳዮች መምሪያ ም/ዳይሬክተርና ኃላፊ ፍራንሲስ ኡዞማ ኦካፎር (ዶ/ር) ፣ በናይጄሪያ ሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን የሕግ መምሪያ ዳይሬክተር ኔስተር ኢኬአጉ ፣ እንዲሁም በሴድረስ ግሩፕ አፍሪካ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ዴሌ አኪንጆን በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የካፒታል ገበያ አስፈላጊነትን አስመልክቶ ያደረግነው ውይይት ተካትቷል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox