Sovereignty Sources

ገልፍ ኦፍ ጊኒ፡ የጂኦፖለቲካ እና ደኅንነት ቁልፍ የትኩረት ቀጠና

Sputnik
''በገልፍ ኦፍ ጊኒ የሚታቀፉ ሀገራት ብዛትና ያላቸው የጂዮ - ፖለቲካ ሁኔታና የውስጥ የፖለቲካ ስርዓተ መንግስቶቻቸውና ድንበራቸውን ያለፉ ጉዳዮችን ጭምር ሊዳኙና ሊተባበሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ነው ወሳኝ ሆነው የሚታዩት [...] ሩሲያ እና ቻይና ተሰሚነታቸው እየጨመረ በመምጣቱ በአፍሪካ ብሎም በቀጠናው ከባህላዊው የምዕራባዊያን አካሄድ በተለየ አማራጭ የአጋርነት መንገድን ይከፍታል '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል የገልፍ አፍ ጊኒ ጂዮ-ፖለቲካ እና በቀጠናው ያንዣበበውን የባህር ላይ ውንብድና፣ የሽብርተኝነት ጉዳይ እና ከአዳዲስ ኃይላት ጋር የሚደረግ ትብብርን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴን በእንግድነት ጋብዘናቸዋል። በፕሮግራሙ ሁለተኛው ክፍልም ሩሲያ ለአፍሪካዊያን ወጣቶች የፈጠረችውን የትምህርት ዕድል በሴንት ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በ3ኛ ዲግሪ የኢኮኖሚክስ ተማሪ አሉላ ተክለብርሃን ጋር ቃኝተነዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox