''ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያሏት የኢንዱስትሪያል ፓርኮች ለሌሎቹ ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችሉ ናቸው — የብሪክስ ማዕቀፍ በአህጉሪቱ ያሉ ሀገራት በዘርፉ የላቀ ደረጃ እንዲደርሱ ትልቅ ዕድልን አመቻችቷል'' ሲሉ በባዮ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የኢንዱስትሪያል ባዮ ቴክኖሎጂ ዳይሮክቶሬት ስር ተመራማሪና የቡድን መሪ ፍሬው ታፈሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ በክፍል አንድ የአፍሪካ ሀገራት በባዮ ኢኮኖሚ ዘርፍ እንዴት በብሪክስ ማዕቀፍ ስር ራሳቸውን ያሥተሳስሩ ስንል በባዮ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የኢንዱስትሪያል ባዮ ቴክኖሎጂ ዳይሮክቶሬት ስር ተመራማሪና የቡድን መሪ ፍሬው ታፈሰ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍልም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከምዕራባዊያን የእርዳታ ድጋፎች ተላቅቀው ውስጣዊ የፋይናንስ አቅማቸውን መገንባት በሚችሉበት ጉዳይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ፣ የኢትዮጵያ አረጋዊያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር ም/ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ክፍሉ እና በሄልፕ ኤጅ ኢትዮጵያ ሲኒየር ፕሮግራም አድቫይዘር ሶፊያ መሃመድ ጋር ቃኝተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox