''በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያሉ ሀገራት የሚጋሯቸው በርካታ ጉዳዮቾ ያሏቸው ሲሆኑ እንደ ማኅበረሰባዊነት፣ ቀጠናዊነት፣ ቋንቋና ባህል ያሉት ተጠቃሾች ናቸው —ኢትዮጵያ በታሪክ በቀጠናው እንዲሁም ከዛም ባለፈ አዎንታዊ ሚናን በመጫወት የምትታወቅ ሀገር ናት ሲሉ '' የውጭ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ የጋራ ፖሊሲዎችና የወደፊት ዕይታዎች ዙሪያ የእርስ በርስ ትስስርና ትብብርን መፍጠርና በቀጠናው የኢትዮጵያን ቁልፍ ሚና በተመለከተ ከውጭ ጉዳዮች ተቋም ምክትል ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንዳስሳለን። የአፍሪካ ሀገራት ለዘመናት ከተጫናቸው የውጪ አካላት ቁጥጥር ለመላቀቅ የራሳቸውን ነፃ ፖሊሲዎች መገንባት አለባቸው በሚል ነዋሪነቷን ታንዛንያ ካደረገችው ደራሲና መምህርት ሚስ ሼቮን ፎርድ ጋር ያደረግነው ቆይታም በዚሁ ፕሮግራም የምንዳስሰው ሌላኛው ዐቢይ ጉዳያችን ነው።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox