''ናይጄሪያ ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት በምዕራብ አፍሪካ ትልቋ ሀገር ነች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንቀፅ 2 በተለይም ንዑስ አንቀፅ 4 የትኛውም ሀገር ሉዓላዊ እንደሆነ ነው የሚያስቀምጠው — ጣልቃ የሚገባባቸውን ሁኔታዎቸችንም በግልፅ ያስቀምጣል'' ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ለሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
አክለውም ፡
''አሁን በዓለም ፖለቲካ አማራጮች እየበዙ ነውና አፍሪካም ቆም ብላ እነዚያን የትብብር አማራጮች መመልከት ይኖርባታል '' ብለዋል።
በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን እንዳስሳለን፡፡ በመጀመሪያው ክፍል አሜሪካ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ ላይ እያሳደረች ያለችው ተፅዕኖ እና ያልተገባ የሉዓላዊነት ጣልቃ ገብነትን ከቀጠናው የጂኦ ፖለቲካ አንፃር ከፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ መምህሩ አለሙ ለሚ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። በክፍል ሁለትም በሀገር ውስጥ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በህዝቦችና ብዝሃ ባህሎች መካከል መቻቻልና መግባባትን ማጓልበት ስለሚሰጠው ፋይዳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ማኅበረሰብ ወይም ሶሺዮሎጃ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰሩ በእውነቱ ዘውዴን አነጋግረናቸዋል ።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox