“[ምዕራቡ ዓለም] ወጥመድ ውስጥ ለማስግባት ይሞክራሉ፣ ምክንያቱም በገንዘብ በሚረዱበት ጊዜ ሁሉ የራሳቸውን መስፈርት ያስቀምጣሉ። የአንተ ፍላጎት በእነሱ ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም።[...] አንተ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ መወሰን አለብህ። ለእነዚያም ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች ከሀገር ውስጥ ገንዘብ እንዲገኝ ማድረግ ይገባል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ጄኔቲክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ደረጀ በየነ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የዘረመል ንቅለተከላ (የጂኖም ኤዲቲንግ) የአፍሪካን የምግብ ስርዓት፣ ሳይንሳዊ ሉዓላዊነት እና የመቋቋም አቅም እንዴት እየለወጡ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ጄኔቲክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ከሆኑት ከ ደረጀ በየነ (ዶ/ር) ጋር የተወያየን ሲሆን፤ ወደ አፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ተሻግረን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በቅርቡ ባደረጉት ንግግር ዙሪያ፣ በቀይ ባህር ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፈር በድሩ(ዶ/ር) እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ የሰጡንን ትንታኔ አካትተናል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox