"በሕክምና አገልግሎታችን የምናየው ነገር ቢኖር በስኳር ህመምተኞች ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መኖሩን ነው — ዓይነት 1 እና ዓይነት 2 ላይ ጭማሪ ይታያል። እንዲያውም ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ13 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።" ሲሉ ጠቅላላ ሐኪም ዶ/ር ሩት ዳኛቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በዓለም-አቀፍ ደረጃ በዛሬው ህዳር 5 የሚከበረውን የስኳር በሽታ ቀንን በማስመልከት በኢትዮጵያ በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የስኳር በሽታ ታማሚዎች ቁጥር መንስኤዎች፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ጠቅላላ ሐኪም ከሆኑት ከዶ/ር ሩት ዳኛቸው ጋር የተወያየን ሲሆን፤ በአፍሪካ ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ስለሚደረገው ጥረት በ አራይዝ አፍሪካ ስብሰባ ላይ ከተገኙት የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ኮሶሎ ፍራንሲስ ፣ የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር አቡባካር ኮምፎ፣ ከአፍሪካ የህጻናት ፖሊሲ ፎረም ዶ/ር ጆኣን ናንዩኪ እና የጋና የጾታ፣ ህጻናት እና ማህበረሰብ ጥበቃ ሚኒስቴር ከሆኑት ከፔሸንስ ሄይፎርድ ጋር ያደረነው ቆይታ በዚህ መሰናዶ ውስጥ ተካተቷል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox