‘‘ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሶሪያ ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ በብሪታኒያ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ ተጀምረው የነበሩ ምርመራዎች በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በድንገት እንዲቋረጡ ሆነዋል፡፡ ለምን ብለህ ብትጠይቃቸው ግን አሳማኝ ምክንያት አይሰጡህም፡፡ ተመሳሳይ ነገሮችን በተለያየ መንገድ የሚዳኝበት መንገድ በጣም የገዘፈ ነው፡፡’’ ሲሉ ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
የዛሬው ድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፡፡ በቀዳሚነት አፍሪካን ማጥቂያ የሆነው በዓለምአቀፉ ወንጀለኞች ፍርድቤት የሚደርስባት አድሏዊ አሰራርና በደልን እንዳስሳለን። ለዚህም የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የአፍሪካ ደራሲያን እና አሳታሚዎች የአህጉሪቱ የባህልና የቋንቋ ሀብቶች ተገቢ እና እውነተኛ እውቅና ያገኙ ዘንድ በአለም አቀፍ መድረኮች ስለሚያሰሟቸው ጥሪዎች እንወያያለን ፤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነጽሁፍ መምህር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox