'' አፍሪካ የጦር መሣሪያ አምራቾች ማራገፊያ፣ ክንደ ፈርጣማዎቹ ጡንቻቸውን የሚለካኩባት ቦታ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲያዊ መድረክ ንቁ ሚና ከመፍጠር ይልቅ ተቀባይ ሆናለች — ይህ ደግሞ ለሱዳንና መላ አፍሪካዊያን ወንድሞች አሰቃቂ ገጠመኝ ነው '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ሌክቸረሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ኃይላት የሚያደርጉት ደም አፋሳሽ ጦርነት ሱዳንን ከድጡ ወደማጡ ከቷታል። ጦርነቱ ሺዎችን ሲቀጥፍ ሚሊዮኖች ከቀያቸው አፈናቅሏል። የቀሩት ደግሞ ሱዳን የምድር ሲዖል ሆናባቸዋለች። የዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን የመጀመሪያ ክፍል ይህን ጉዳይ በሰፊው ለመዳሰስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩን የእዮብዘር ዘውዴን በእንግድነት ጋብዘናቸዋል።
በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ጉባዔ እንዲሁም የፓን አፍሪካ ቱሪዝም ልዑካን ከአቡጃ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ በተመለከተም ከአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና ፓሲፊክ ፓርላማ ዳይሬክተር አምባሳደር ዮንግ ፔይሮ ኦማትሺዬ (ዶ/ር) ጋር የተደረገው ቆይታም ሌላው ጉዳያችን ነው።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox