“ግብርና ላይ የተመሰረተ የወጣቶች የስራ እድል እየፈጠርን ነው፡፡ በትንሽ ገንዘብ በጣም ብዙ ወጣት ነው ስራ የምናስይዘው፡፡ ወደ 611 ሺ ወጣት ነው ስራ ልናስይዝ በ 5 ዓመት ውስጥ ፈንድ የወሰድነው፡፡ አንዱን ዓመት አጠናቀናል፡፡ ከዚህ ውስጥ 80 በመቶው ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) ጋር ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ እና የፖሊሲ ለውጥ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች እርሻዎች እንዴት የብሔራዊ ዕድገት ሞተሮች ሊያደርጋቸው እንደሚችል እንመለከታለን። ትራንስፎርሜሽኑ በመጨረሻ ወደ ገበሬው እርሻ ሊደርስ ይችላል?
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡