Drum of Changes

ከምዕራቡ ዓለም ባሻገር- ኢትዮጵያ ለቱሪዝሟ እድገት ወደ ደቡባዊው ዓለም ታማትራለች

Sputnik
"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉ አቅፋ ይዛለች ። ስለዚህ አንድ ሰው አፍሪካን በእውነት መጎብኘት ከፈለገ፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሁሉንም ማየት ይችላል።[…] ስለዚህ፣ በብሪክስ ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገሮችን፣ ጥሩ የህዝብ ብዛትን እና ጥሩ ኢኮኖሚን በተመሳሳይ ጊዜ እናገኛለን፤ ይህም እነርሱን የቱሪስት እንግዶቻችን ልናደርጋቸው ያስችለናል።[...] ስፑትኒክ አፍሪካ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ብዙዎች ጋር ለማድረስ ይረዳናል። ሚዲያው ቢሮውን በኢትዮጵያ መክፈቱም ከራዕያችን ጋር በእጅጉ የተጣጣመ ነው" - ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን አነጋግሮ የኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች ሀገራት ጭምር በማዞር አዲስ የቱሪዝም የገበያ እያማተረች ስለመሆኗ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን ይዳስሳል። እንዲሁም ቻይና በቅርቡ ለአፍሪካ ሀገራት '' እተገብረዋለሁ'' ያለችውን የዜሮ ታሪፍ ጉዳይ ያነሳል። ለዚህም የፓን አፍሪካ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ክቡር ገናን አነጋግሯል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።