“አፍሪካ የተባረከች አህጉር ናት፡፡ [...] በጣም ለምና ድንግል መሬት፣ የውሃ ሀብትና የተፈጥሮ ሀብት ሁሉም ነገር አላት። በዘመናዊ መንገድ የተማሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ሌሎች ቦታዎች የሌላቸውን ባህላዊ እውቀት ያላቸው ሰዎችም አሉን። ስለዚህ ጊዜው ሳይረፍድ፣ የራሳችንን ትርክቶች መስራት አለብን። [የተሳሳቱ ትርክቶችን] ማፍረስ እና እንደገና መገንባት በጣም አስፈላጊ ነው።” ዶ/ር ገለታ ሲሜሶ
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ዓለም አቀፍ የሰላም ቀንን በማስመልከት የሰላም አማካሪ ከሆኑት ዶ/ር ገለታ ሲመሶ ጋር ውይይት አድርገናል። ለአፍሪካ ሰላም የጦር መሳሪያ ዝምታ ብቻ ሊሆን እንደማይገባና ሰላምን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ነጻ ስለማውጣትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ተወያይተናል፡፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify