The Rising South

የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር፣ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ያገኙት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች

Sputnik
“ይሄ ምርት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በአፋር ክልል ተሸጦ በቆላና መስኖ አካባቢ ሚኒስቴር ገዢነት ወደ ሁለቱ ክልል ቴክኖሎጂው እንዲተገበር ተደርጎ ሁለቱም ክልል ላይ ቴክኖሎጂውን ሰርተን አምርተን ገጥመንላቸው እየተጠቀሙ ነው።” የወርቅ ተሸላሚ ዘላለም እንዳለው
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቅርቡ ከብሪክስ አባል ሀገራት በተውጣጡ 300 ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች መካከል በቻይና በተካሄደው የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ዘርፎች በመሳተፍ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ከተሸለሙት ሶስት ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያ ወጣቶች ከወርቅ ተሸላሚ ዘላለም እንዳለው፣ ከብር ተሸላሚዉ አቤኔዘር ተከስተ እና ከነሃስ ተሸላሚዋ ነቢሀ ንስሩ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ወጣቶቹ በውድድሩ ላይ ይዘው ስለቀረቧቸው የፈጠራ ስራዎች፣ በውድድሩ ላይ ስለገጠሟቸው ነገሮች እንዲሁም ወደፊት ስላሏቸው ራዕዮች በሰፊው ተወያይተናል፡፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsAfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify