የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዝ የፀጥታው ምክርቤትን ማሻሻል ሙሉ ስሜት የሚሰጥ (አሳማኝ) ነገር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ ለአፍሪካ ምን ማለት ነው?
''አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫን ማግኘት በርካታ አንኳር ጥቅሞች ይሰጣል። አፍሪካን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ድምጿን ማሰማት ትችላለች። የሚጎዳቸው ከሆነ ማገድ ይችላሉ፣ የሚጠቅማቸው ከሆነ ደግሞ ማስተላለፍ ይችላሉ'' - ጃራ ሳሙኤል ቱራ በአርሲ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር
የትምህርት ክፍሉ ዲንና መምህር አበራ ለሚ በበኩላቸው፡-
''[አፍሪካ] ቋሚ መቀመጫ ማግኘቷ ከምጣኔ ሀብት አኳያ ካየነው የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን በመሣብ ከሌሎች ዓለማት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ይረዳታል '' ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ በይበልጥ መሰማት ስለሚችሉባቸው አግባቦች፣ እንዲሁም 80ኛ ዓመት ምስረታውን የሚያከብረው ድርጅቱ የተጣለበትን አደራ መወጣት እንዲችል በምን ዓይነት ሁኔታዎ ከፍተኛ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባል በሚሉ ጉዳዮች የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በአርሲ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል ዲን የሆኑት አበራ ለሚና የትምህርት ክፍሉ መምህር ጃራ ሳሙኤል ቱራን ጋብዟቸው በጥልቀት አወያይቷቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify