The Main Stage

የአፍሪካ ድምፅ በዓለምአቀፍ መድረክ

Sputnik
በፈጣን የዓለም እንቅስቃሴ ውስጥ፣ ባህሎች የመደብዘዝ እና የመገደብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
[አፍሪካዊያን ] ከዓለም ጋር በአብሮነት መስራት አእንዳለ ሆኖ ፣ የቤት ስራችን ባህላዊ ማንነታችንን ማስጠበቅ ነው - አምባሳደር ነብዩ ተደላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር
የኢንተርቪዥን 2025 የሙዚቃ ውድድርም የፊታችን መስከረም 10 ፣ 2018 ዓ.ም በሩሲያ ሞስኮ ይካሄዳል፡፡
“ይህ ውድድር ብቻ አይደለም፣ የተዛቡ አመለካከቶችን የሚዋጋ እና ሙዚቃችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፋዊ መድረክ ነው።” ድምጻዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ
የዛሬው የሜን ስቴጅ ዝግጅታችን ባህልን እና ሙዚቃን በሰፊው ይዳስሳል ፣ ለዚህም በሴንት ፔተርስበርግ 11ኛውን ዓለም አቀፍ የተባበሩ ባህሎች መድረክ የተሳተፉትን በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ነብዩ ተደላ ፣ የኢነተርቪዥን 2025 ዉድድር ተሳታፊዎችን ድምጻዊት ነጻነት ሱልጣን ከኢትዮጵያ ፣ ዲ ሊያን እና ዴኒስ ከ ማዳጋስጋር ፣ የደቡብ አፍሪካዎቹን ማዛኒስ ጃኬሌሌ ቡድን የሞስኮ ባልደረቦቻችን አነጋግረዋቸዋል ። የኮራ እና አፍሪማ የሙዚቃ ውድድር አሸናፊዋን ድምጻዊት ፀደንያ ገብረማርቆስንም ስለሙዚቃ ውድድሩ ጠቀሜታ

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify