“በአረንጓዴ አሻራው ደስተኛ ነኝ፣ እናም የኢትዮጵያን አርአያነት በመከተል ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ቢያንስ በወር አንዴ ተግባራዊ ልናደርገው የተገባ ነው'' ሲሉ ሚስ ጆይስ ሜንዴዝ ኮል ተናግረዋል።
በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በኢትዮጵያ ለተከታታይ ዓመታት እየተተገበረ ያለውን የአረንጓዴ አሻራን፣ የአፍሪካ የሴቶች ቀን እና ስለ ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች በሶስት ክፍሎች ለመወያየት የአፍሪካ የሴቶች አመራር ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ሚስ ጆይስ ሜንዴስ ኮልን ጨምሮ በርካታ እንግዶችን ጋብዟቸዋል።