“የጤና ስርዓት ቱሪዝምን መገንባት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የሰው ኃይልን መገንባት ስለሚኖርብን። ብዙ ሙያተኞቹን እያበቃን ነው። ብቃት ያላቸው በርካታ ሀኪሞች እየተፈጠሩ በመሆናቸው በየቦታው ሙያቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ መሠረተ ልማቶችና ማዕከላት ለጠቅላላ ሀኪሞችና ስፔሻሊስቶች ምቹ ከሆኑ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ በርካታ የውጭ ዜጎችን ለህክምና እንዲመጡ ማድረግ ይቻላል" ብለዋል የኢትዮጵያ ጋስትሮኢንትሮሎጂ ማኅበር ኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊው ዶ/ር ካሳ ታምሩ።
በርካታ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች በተለይም እንደ ጅቡቲ፣ ሱዳንና ሶማሌ ላንድ ያሉት የተሻለ ህክምና ለማግኘት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኢትዮጵያን ተመራጭ እያደረጓት ነው ።
በህክምና ቱሪዝምና ተያያዥ ጉዳዮች የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢ የኢትዮጵያ ጋስትሮኢንትሮሎጂ ማኅበር ኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊው ዶ/ር ካሳ ታምሩ፣ የላንሴት ሆስፒታል ማዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አቤል ሀይሉ፣ የኦፕታልሚክ ሰርጅን ኮርኒያ የዓይን የውጭ ክፍል ህመም ሰብ - ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ኤሌያስ እና የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ሀኪሙ ዶ/ር መሃመድ አወል አህመድን በጥልቀት አወያይቷቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify