“ሀሳቤ ለሞቃታማ ሥፍራዎች ተስማሚ ጥሩ የግንባታ መሣሪያ ማምራት ነበር። ስለዚህ ዋናው ሀሳቤ ከሄምፕክሪት ግንባታ ነበር የመነጨው። ከዛ ነበር ቴክኖሎጂውን የቀዳሁት። ፕሮስክሪት ወደተባለው የራሳችን ምርት ነበር የቴጂክኖሎጂ ሽግግር የተደረገው” ሲል ሲቪል መሃንዲሱ ሱራፌል በላይ ተናግሯል።
'ጁሊፍሎራ' በኢትዮጵያ በረባዳማ ሥፍራዎች ወይም በቆላማ አካባቢዎች የብዝሃ ህይወትን የሚያዛንፍ የአርሶ አደርና አርብቶ አደሩን ህይወት እየጎዳ ያለ መጥፍ ዕፅ ነው። ይህን ተክል ለማስወገድ ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። በዚህ ረገድ የሶቨርኒቲ ሶርስስ አቅራቢ በተለምዶ 'የወያኔ ዛፍ' ተብሎ የሚጠራዉን 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' ን ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የለወጠው የሲቪል ምህንድስና ባለሙያው ሱራፌል በላይን በመጋበዝ ጥልቅ ወይይት አከናውኗል።
የፀሐይ እና ታዳሽ ኃይል በተመለከተ ከኢትዮጵያ የፀሐይ ሃይል ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ የምሥራች ሲሳይ ጋር የተደረገው አጭር ቆይታም የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify