“የዲጂታል መሩ ጤና የወደፊቱ የዓለም ስርዓተ ለውጥ ነው። ፕላኔታችን የዓለም ምጣኔ ሐብት ነው። የዲጂታል መር ጤና ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ ነው። የእናቶች ሞት፣ ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች፣ በፅኑ ህመም ያሉ ህመምተኞች ባሉበት ሁኔታ የዲጂታል መር ጤና ተግዳሮቶቹን የመቋቋሚያ ሁነኛ መላ እየሆነ መጥቷል” ሲሉ የፓን - አፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማኅበር ዋና ኃላፊ ዶ/ር ሶስተንስ ባጉሜምሄ ተናግረዋል።
ዶ/ር ሶስተንስ አክለውም፡-
“የእርዳታ ድጋፍ መቋረጥ የዓለማችን ዋነኛ እክሎች ቢሆኑም የተለያዩ ዲጂታል መር የጤና ባለድርሻዎች እንዳተባበሩ በማድረግ በዋሻው ጫፍ ላይ ጮራ እንዲፈነጥቅ የሚያደርግ ነው'' ብለዋል።
በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የእርዳታ መቋረጥን ተከትሎ የሚመጡ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም ለሁሉም ብሩህ የወደፊትን ለመፍጠር የእርስ በርስ ትብብርና ፈጠራ ስለሚያበረክቷቸው ቁልፍ ሚናዎች ለመወያየት የፓን - አፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማኅበር ዋና ኃላፊ ዶ/ር ሶስተንስ ባጉሜምሄን እና ሌሎች የአህጉሪቱ የጤና ዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ጋብዟቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify