"የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእናቶች ሞት ጉዳይ በትኩረት ሲሰራ የተሻለ በጀት፣ ትኩረት፣ የስልጠና ዕድሎች፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ የጤና ባለሙያዎችን በጎለበተ እውቀትና መሠረተ ልማት ማስታጠቁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል። የእናቶች ሞት ብዬ መናገር እችላለሁ። ለዚህም ሁልጊዜም አመስጋኞች ነን። አንዲት እናትን ማዳን አንድ ቤተሰብ እንደመታደግ ነው'' ሲሉ የጽንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ዶ/ር ምስክር አንበርብር ተናግረዋል።
በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በወሊድ ሆነ በድህረ ወሊድ ወቅት ስሚፈጠር የእናቶች ሞት፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለችውን አበረታች ሥራዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመወያየት የጽንስና የማህፀን ስፔሻሊስቶቹን ዶ/ር ምስክር አንበርብር እና ዶ/ር ታጠቅ ተስፋዬን ጋብዟቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify