"ከአውሮፓውያኑ እና ዩክሬን የበለጠ አስፈላጊው የሩሲያ እና የአሜሪካ ንግግር ስለሆነ ዩክሬን ብቻ ሳትሆን አውሮፓውያኑም ከዚህ ሂደት ውጭ ናቸው። ስለዚህ ትራምፕ ራሳቸውን አጋር ለማድረግ ከሌሎች ኃይሎች የበለጠ ጠንካራ ከሆነችው ሩሲያ ጋር ለመነጋገር ብልህ መሆንን የተረዱ ይመስለኛል" ሲሉ የታሪክ ምሁሩና የፖለቲካ ተንታኙ ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ተናግረዋል።
በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ በሚያደርጉት ተጠባቂ ስብሰባ በሰፊው ይዳስሳል።
በስብሰባው የሚነሱ አንኳር ጉዳዮች ፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦች ለመወያየት ፕሮፌሰር አየለ በክሪ ፣ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ እንዲሁም ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ፣ የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ እና ጉምቱው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጋብዟቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Afripods – Deezer – Pocket Casts – Podcast Addict – Spotify