የኢትዮጵያ የፋሽን ኢንደስትሪ ፈተና መልኩ እንዲህ ነው “ድሮ የቦንዳ ልብሶችን ሰው ተሸማቆ ነበር የሚገዛው [...] አሁን ግን ትልልቅ ሞሎች ላይ የቦንዳ ልብሶች ይሸጣሉ።” ስትል ዲዛይነር ኢክራም መሐመድ ነግራናለች።
ከዚህ መውጫው መንገድ ደግሞ የህንድ ምሳሌ ነው። "የኢትዮያ ታምርት ፅንሰ ሃሳብን ማስረፅና በኢትዮጵያ ምርት የምንኮራበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፣” ሲል በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲትዩ አፓረል ዲን ቢኒያም ሰለሞን ነግሮናል።
በዚህ The Rising South የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በሞስኮ የሚካሄደውን አፍሮ ፋሽን ሳምንት 2025 መነሻ አድርገን ከባለሙያዎቹ ጋር ዕድልና እንቅፍቶችን አንስተን በሰፊው ተወያይተናል።