የአፍሪካ ትምህርት በቅኝ ግዛት ከመታወኩ በፊት በአገር በቀል እውቀት የተቀረፀ ጥልቅ፣ የተለያየ ታሪክ ያለው ነበር። ዛሬም አህጉሪቱ የራሷን እሴቶች እና እውነታዎች ለማንፀባረቅ ከቅኝ ግዛት ዘመን የተወረሱ ስርዓቶችን የመቀየር ፈተና ተጋርጦባታል።
በዚህ የራይዚንግ ሳዉዝ መሰናዶም የሚዲያ እና ትምህርት ለልማት አፍሪካ ፎረም ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ላዋሊ ኮል ጋር ያልተነገረውን የአፍሪካን ትምህርት ታሪክ ፤ የቅድመ ቅኝ ግዛት የእውቀት መገለጫዎችና፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ጥፋቶችን በሰፊው እንመረምራለን።
ዶ/ር ላዋሊ ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገሩ፦
“ከቅኝ ግዛት በፊት የአፍሪካ ትምህርት በጋራ መሰርቶች ላይ፣ ተግባር ተኮር እና በእሴቶች ላይ የተመሰረተ ነበር። ይህ ዛሬ እንደምናየው በመደበኛ ትምህርት ቤቶች የተደራጀ ባይሆንም ያን ያህል ውጤታም አልነበረዉም’’ ብለዋል፡፡
“በቅኝ ግዛት ስር የነበረው ትምህርት የቁጥጥር መሳሪያ ነበር’’ የሚሉት ዶ/ር ላዋሊ በዚህ መንገድ ጫና ውስጥ የቆየውን የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ለመቀየር አህጉሪቱ አለምዓቀፍ ትብብርን ማድረግ አለባት ፤ ለዚህም ብሪክስ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
‘‘ብሪክስ አዲስ ነው ፣ ባለፉት ዓመታት ካየነው አንፃርም ብሪክስ በአፍሪካ ልማት ላይ ከአፍሪካ ጋር ከሚሰሩ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትም አንፃር ቢሆን የተለይ እይታ አለው፡፡ አሁን እንደምታየው የዪኤሳይዲ ድጋፍ ሲቋረጥ […] በአፍሪካ ብዙ ጫና ፈጥሮ እንደተመለክትነው ፣ ዩኤስኤአይዲ በብሪክስ ፅንሰ ሃሳብ ቢሰሩ ኖሮ ‘ሁልጊዜም አሳዉን ከምሰጥህ አሳ አጠማመዱን አሳይሃለሁ’ የሚል ቢሆን ኖሮ ዛሬ [አንጎዳም ነበር] ፡፡ […] ለዚያም የብሪክስ ኢኒሼቲቭ ይበል የሚያሰኝ ነው’’ ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን የራይዚንግ ሳውዝ ፕሮግራም ይከታተሉ!