The Rising South

የኢትዮጵያ ብዝኃ-ሕይወት እና ሉዓላዊነት:- ከተፈጥሮ ጋር  የመስማማት መንገድ

Sputnik
በራይዚንግ ሳውዝ ፣ ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀንን ስናስብ ከኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት የመጡ ባለሙያዎችን ወሳኝ ሀሳቦች እናደምጣለን ።

"ከ83,000 በላይ ናሙናዎች በቀዝቃዛ ክፍል እንዲሁም ከ9,000 በላይ የሚሆኑ ዝርያዎች በመስክ የዘረ-መል ባንክ ውስጥ ተጠብቀዋል።" ሲሉ አቶ ውብሸት ተሾመ ተናግረዋል ።

አክለውም ከሩሲያ ጋር በዘረ-መል ልውውጥ፣ በእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የዳበረ ትብብር ሊፈጠር ይገባል ብለዋል።
ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ በበኩላቸው "የዘረ-መል ዝርፊያን ለመከላከል የወጣውን የናጎያ ስምምነትን ተከትሎ አፍሪካውያን የብዝኃ-ሕይወት ሀብትን ለመጠበቅ ትብብር ማድረግ አለባቸው  ፤ በዚህም ለውጥ ማምጣት እንችላለን '' ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ባላት ታሪካዊ የብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ትስስር ፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያን የሰብል ልዩነቶች ላይ በርካታ የጥናትና ምርምር ግኝቶችን ያበረከተው ሩሲያዊዉ ሳይንቲስት ኒኮላይ ቫቪሎቭ ሁልጊዜም ሲታወስ ይኖራል ብለዋል ባለሙያዎቹ።
የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ቅርስ ሀብት እና በዓለም-አቀፍ የብዝኃ-ሕይወት ወስጥ ያላትን የአመራር ሚና በጥልቀት ለመረዳት ይህን ፕሮግራም ይከታተሉ።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify