ይህም በመዲናዋ ውስጥ የተገነቡትን የመኪና ማቆሚያዎች ቁጥር ወደ 150 ከፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
ከለውጡ በፊት በመንግሥት የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ብዛት 2 ብቻና ከ500 በላይ መኪኖችን የማቆም አቅም እንዳልነበራቸው በማሕበራዊ ገጻቸው ባጋሩት ፅሑፍ ጠቁመዋል።
ከንቲባዋ በአጠቃላይ 35 ሺህ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችሉ እንዲሁም 49 ተርሚናሎች መገንባታቸውን ገልጸዋል።
አዲሱ የመኪና ማቆሚያ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት እንዲሁም የሕዝቡን እንግልት የሚቀንስ መሆኑ ተገልጿል።