የኢትዮጵያ መንግሥት ገለልተኛ መርማሪዎችና መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ በአስቸኳይ እንዲፈቅ

የኢትዮጵያ መንግሥት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ባለሙያዎች ኮሚሽን እና መገናኛ ብዙኀን የግጭት ቀጠና ወደሆነው አማራ ክልል እንዲገቡ ባስቸኳይ እንዲፈቅድ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
Sputnik
አምነስቲ ትላንት ባወጣው መግለጫ በክልሉ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል ሲል ጠቅሶ በፍኖተሰላም፣ ባሕርዳርና ሸዋሮቢት የጅምላ ግድያዎች መፈፀማቸውን መረጄዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡
“በመሆኑም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ባለሙያዎች ኮሚሽን እና መገናኛ ብዙሀን ወደ ክልሉ ገብተው ምርመራ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀድ አለበት” ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ ገልፀዋል፡፡
አክለውም መንግሥትና ጸጥታ ኃይሎች ሰብዓዊ መብቶችን መጠበቅና ማክበር አለባቸው ሲሉ ቲጌሬ አሳስበዋል፡፡