ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡
''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የፋሺስት ጣሊያን ዳግም ወረራ ምክንያቶች፣ የአውሮፓ ኃያላን በአፍሪካ የነበራቸው የተዛባ ፍላጎት፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ የዲፕሎማሲ ውድቀት እና የኢትዮጵያ አርበኞች ለአምስት ዓመታት ያሳዩትን ጽናትና በድል የተጠናቅቀውን ድል አስመልክቶ ፣ የታሪክ ምሁሩ ጥላሁን ጣሰው እና በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህ አብዲ ወርቅነህን አነጋግረናቸዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox