አሜሪካ ወዴት እየሄደች ነው፦ የአንድ ኃያልነት ማብቂያ ወይስ በምርጫ የመጣ ጥፋት?

Sputnik
"ወጥመድ" የሚለው ቃል፤ ዶናልድ ትራምፕ በቤንጃሚን ኔታንያሁ ግፊት ከኢራን ጋር በተያያዘ የገቡበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመግለጽ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
አሌክሳንደር ያኮቬንኮ፣ የሮሲያ ሴጎድንያ (የስፑትኒክ እናት ኩባንያ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር እናየሩሲያ የደኅንነት ምክር ቤት የሳይንሳዊ-ኤክስፐርት ቦርድ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ደኅንነት ኮሚቴ ሰብሳቢ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ያለውን የቅርብ ጊዜ ቀውስ ያብራራሉ።
ይሁንእንጂ ሁኔታውን ይበልጥ በትክክል ለመግለጽ፦ የአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም ላለፉት 10 እና 15 ዓመታት የፖለቲካ አክራሪነት ከነገሰባት እስራኤል ጋር እጅግ ከመቆላለፉ የተነሳ የመጣ ውጤት ነው ማለት ይቻላል። ይህ "ወጥመድ" የዘመናዊቷን አሜሪካ የነገ እጣ-ፈንታ የሚወስን ሊሆን ይችላል። ዋሽንግተን በጋዛ እና በሊባኖስ ጉዳይ ላይ ቴል አቪቭ እንደምትከተለው ዓይነት የሃይል እርምጃ መውሰድ አትችልም፤ ምክንያቱም ይህን ካደረገች በሁለቱ ሀገራት የፖሊሲ ልዩነት ላይ ያለው ቀጭን መስመር በማይመለስ ሁኔታ ይጠፋል። ይህም ማለት እስራኤል ወደ አሜሪካ የልዕልና ደረጃ ትወጣለች ማለት ሳይሆን፣ አሜሪካ ወደ እስራኤል መጠነ-ጠባብነት ትወርዳለች ማለት ነው። የአሜሪካ የፖለቲካ ልሂቃን እና በኢራን ጉዳይ ላይ በቀጥታ የተሳተፉ አካላት (ወታደራዊ አመራሮችን ጨምሮ) ይህንን አደገኛ ቁማር ሳይገነዘቡት አይቀሩም። እስራኤል ራሷ እንደምትቀበለው፣ በዚህ ሂደት ውስጥ "አሜሪካን እያጣቻት" ትገኛለች።
ዋሽንግተን የኢራንን ፖለቲካዊ አመራር ለማጥፋት በገባችው ቃል ኪዳን ምክንያት ከእስላማዊአብዮታዊ ዘብ ኃይል(IRGC) ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጣለች። አሁን ግን ከዚሁ ኃይል ጋር በገባችበት የዉክልና ድርድር ይህንን የኢራን ፖለቲካዊ ሥርዓት ቁልፍ አካል ሕጋዊ ዕውቅና ለመስጠት ተገድዳለች። ከዚህም በላይ፣ በአሜሪካውያን ዘንድ በአሸባሪነት የተፈረጀው ይህ (የኢራን ፖለቲካዊ) ክንፍ፣ አሁን ያገኘውን ታሪካዊዕድል ለመጠቀም ቆርጦ ተነስቷል። ይህም ዕድል በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን አሜሪካ-ተኮር ሥርዓት መቀየር ብቻሳይሆን፣ መላውን የአሜሪካ ዓለም አቀፋዊ የአንድየበላይነት ለማክሰም የቀረበ በአሁኑ ወቅትም ይህ ኃይል የበላይነቱን እያረጋገጠ ባለበት ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚህ በአዲሱ ጎልያድ (አሜሪካ) እና በቴህራን መካከል በሚደረገው ፍልሚያ፣ ዕጣ ፈንታ ለቴህራን የብሉይ ኪዳኑን ዳዊት ሚና ትሰጣለች ብሎ ማን በገመተ ነበር?
አሁን ላይ ግን የኢራን "የኒውክሌር ቦምብ" ተብሎ በትክክል ሊጠራ የሚችለውን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት፣ ቴህራን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት እንዲከሰት ማድረግ ትችላለች። ይህ ደግሞ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ አስከፊ መዘዝ የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ የፔትሮ-ዶላር ሥርዓቱን ራሱን ከሥር መሠረቱ የሚንድ ይሆናል።
ቻይናከአረብ ባሕረ ሰላጤ አገራት ነዳጅን በዩዋን መግዛት ከጀመረች ሰነባብታለች፤ አሁን ግን የኃይል መሠረተ ልማቶቻቸው ከወደሙ በኋላ (ወታደራዊ ግጭቱ ዳግም ከተቀሰቀሰ ውድመቱ ሙሉ በሙሉ ሊሆን ይችላል)፣ እነዚህ አገራት ለዳግም ግንባታም ሆነ ለሰላማዊ ኑሮ የሚሆናቸው ያው የለመዱት ዶላር እጃቸው ላይ የለም። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ (Fed) ጋር የገንዘብ ልውውጥ መስመር (Swap line) እንዲመቻችላት ጠይቃለች፤ ይህ ካልሆነ ግን ወደ ዩዋን ለመቀየር ትገደዳለች። ይህ ደግሞ ስልታዊ አሰላለፍን ወደ ቤጂንግ ማዞር ማለት ሲሆን፣ ትርጉሙም "ደህና ሁኚ አሜሪካ!" ማለት ነው። የግል ቂም የለበትም! ሁሉም ነገር በጥሬውም ሆነ በምሳሌያዊ አነጋገር "በአሸዋ ላይ የተገነባ" ሆኖ አርፎታል። ታዲያ ይህንን ሁሉ ለማጣት ለምን እንዲህ ዓይነት አደገኛ ቁማር መጫወት አስፈለገ?
አሁን ዋሽንግተን በሁለት አማራጮች መካከል ቆማለች፦ የመጀመሪያው፣ በኢራን ላይ ሁለተኛ ዙር ጥቃት መሰንዘር ነው። ኢራን ይህንን ጥቃት በግልጽ ትፈልገዋለች፤ ምክንያቱም የግጭቱ ውጤት የመጨረሻ ሊሆን የሚችለውና ዲፕሎማሲያዊ ባልሆነ መንገድ እልባት የሚያገኘው በኃይል የታጀበ እርምጃ ሲወሰድ ብቻ መሆኑን ትረዳለች። ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ፣ በተለያየ ሽፋን የኢራንን ቅድመ ሁኔታዎች በመቀበል፣ ያለምንም ካሳ ክፍያ ከአካባቢው በዝምታ መውጣት ነው።

ይህ አማራጭ ሪፐብሊካኖች በመጪው የኅዳር ወር አጋማሽ ምርጫ (Midterm elections) ሁሉንም ነገር ሳያጡ፣ ለ"MAGA" (Make America Great Again-አሜሪካን ዳግም ታላቅ ማድረግ) መራጭ ዜጎቻቸው ፊታቸውን እንዲመልሱ ዕድል ይሰጣቸዋል። ያም ሆነ ይህ ግን፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ የቁጥጥር ሥርዓት ውሳኔ እና አስተዳደር በኢራናውያን እጅ መውደቁ የማይቀር እውነታ ነው።

አሜሪካበአሁኑ ወቅት ያለችበት ምርጫ ወይ በእሷ ላይ ያለውን አመኔታና ክብር ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋ፣ አሊያም ደግሞ ያንን ክብር ዳግም የሚያድስ ነው። ይሁን እንጂ ክብሯ ሊመለስ የሚችለው አንድ ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታ ሲሟላ ብቻ ነው፦ ይህም አሜሪካ እንደ ቀደመው 'ተቀዳሚ ዓለም አቀፍ ኃይል'ነቷን የምታረጋግጠው በሌሎች ሀገራት ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር ሳይሆን፣ በራሷ የቴክኖሎጂ ብቃትና የልማት ስኬት መሆኑን በየጊዜው በተግባር ስታስመሰክር ነው። ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ሌላውን ዓለም በመበዝበዝ ወይም በሌሎች ኪሳራ ላይ የተመሰረተ ህልውናን ፈጽሞ ስትተው ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ባለፉት አሥርተ ዓመታት እንደታየው ሁሉ፣ አሁንም ምንም ዓይነት ለውጥ ሊመጣ አይችልም። በነዚያ ዓመታት የአሜሪካ ልሂቃን፤ በብዙ የሚከበረውና የሚነገረው 'መሪነታቸው' ለዘላለም የተሰጠ መለኮታዊ ስጦታ እንደሆነና ይህንንም በተግባር ማረጋገጥ እንደማያስፈልጋቸው በስህተት ያምኑ ነበር። ከሃያ ዓመታት በፊት ብርዜንንስኪ እንደጻፈው፤ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላትን የበላይነት ጠብቃ ለመቀጠል ከፈለገች፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ 'ከብሄራዊ ጥቅሜ' በላይ የሆነ ሰፊ ራዕይ ሊኖረው ይገባል። ይህ የወደፊት የዓለም እጣ-ፈንታ ራዕይም ሌሎች ሀገራት በፈቃደኝነት የሚጋሩትና አብረውት የሚቆሙት መሆን ይኖርበታል።
ከኢራን ጋር ለተፈጠረው ግጭት ምላሽ መስጠት የሚችሉት አሜሪካውያን ብቻ ናቸው። የቀሩት ሁሉ፣ አጋሮቻቸውን ጨምሮ፣ ራሳቸውን ከጉዳዩ አግልለዋል። ይህ ራቅ የማለት ወይም 'ጉዳዩ አይመለከተኝም' የማለት አዝማሚያ (እንደ ጣሊያኖች 'ፋርኒየንቴ'—ምንም አለማድረግና መዝናናት ዓይነት ስሜት) ወታደራዊ ኃይል ከሚያመጣው ጥፋት ባልተናነሰ ኔቶን (NATO) ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል። ይህ አይነቱ 'ቸልተኝነት' በራሱ እንደ ኢራን 'ሰላማዊ የኒውክሌር ቦምብ' ሊቆጠር የሚችል አደገኛ መሳሪያ ነው። በዩክሬን ግጭት ወቅት በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲከሽፍ ያደረገውም፤ የደቡብ እና የምስራቅ ዓለም ሀገራት (Global South and East) ከአሜሪካና ከምዕራባውያን ፖሊሲ ጋር አብረው ላለመቆም የወሰዱት ግዴለሽነትና ራቅ የማለት አቋም መሆኑን ማስታወስ ይገባል።
አሁንምቢሆን "የሥልጣኔዎች የማጥፋት ጦርነት" (Civilizational war of annihilation) ተብሎ ሊጠራ የሚችል ሁኔታ አለ (ይህንን ሁኔታ በ1941-1945 የጀርመን ናዚዎች "በሰለጠነችው አውሮፓ" ስም ሲንቀሳቀሱ አይተነዋል።) ይህም ማለት ሰብአዊ ሕግጋትን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ውጭ መሆን ማለት ነው። የ“ፓላንቲር” (Palantir) ኩባንያ ባለ 22 ነጥብ ማኒፌስቶም የሚያጠነጥነው በዚህ ሐሳብ ላይ ሲሆን፤ ይዘቱም የፖለቲካ ውሳኔዎችን ሥነ-ምግባራዊ ገጽታ በመተው፣ በሌሎች ሥልጣኔዎች ለሚወከሉ ጠላቶች "አንዳንድ ባህሎች ስኬታማ ናቸው፣ ሌሎቹ ግን ተንኮለኞች (malicious) ናቸው" በሚል መነሻ በጭካኔ እርምጃ መውሰድን ይጠቁማል። ኢራን እና ሩሲያም ከእነዚህ ጠላቶች መካከል ተጠቅሰዋል። ይህ በሰው ሰራሽ አስተዉሎት ላይ የተመሰረተ ወታደራዊ አክራሪነት ግልጽ የሆነ የጦርነት 'ሰብአዊነት አልባነት' መገለጫ ነው። 'እሱ ይዋጋ!' የሚለው መርህ፤ ጦርነትን ከሰው ልጅ ስሜትና ርህራሄ በማራቅ እንደ ማሽን ስራ ብቻ የሚቆጥር ሲሆን፣ ይህ አሜሪካ ቀደም ሲል በድሮን ጥቃቶች ላይ ተመስርታ 'በሽብር ላይ ጦርነት' ስትጀምር የገባችበት አደገኛ መንገድ ማሳያ ነው።ይህ አምባገነናዊ አካሄድ፤ በአሌክስ ካርፕ 'የቴክኖሎጂ ሪፐብሊክ' (technological republic) ጽንሰ-ሃሳብ እንደሚገለጸው፣ በታላላቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (Big Tech) የሚመራ አዲስ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታጠቀ 'ኮርፖሬት መንግስት' የመፍጠር ግብ አለው። በዚህ አዲስ ሥርዓት ውስጥ ደግሞ፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቹ እንደ 'ካህናት' የሚቆጠሩና ከማንም በላይ ሁሉንም ነገር የምናውቅ እኛ ነን የሚል እብሪት የተጠናወታቸው ናቸው። ዓለማችን በአውሮፓ ፋሺዝም እና ናዚዝም ወቅት ስለ 'ኮርፖሬት መንግስት' (መንግስትና ግዙፍ ኩባንያዎች አንድ የሚሆኑበት ሥርዓት) በቂና አስከፊ ልምድ አላገኘችም ወይ? በግል ኩባንያዎች ይተዳደሩ የነበሩ የቅኝ ገዥ ግዛቶችስ ከዚህ በምን ይለያሉ? ለአብነት ያህል፣ ታዋቂው የብሪታንያ ምስራቅ ህንድ ኩባንያ (British East India Company) ህንድን ለ1857ቱ የሲፓይ አመጽ (Sepoy Mutiny) እስከዳረገችበት ጊዜ ድረስ የፈጸመችው ግፍ ትልቅ ማሳያ ነው። ያኔ ለትርፍ ብቻ የሚሰሩ የግል ኩባንያዎች ሀገርን እንዲያስተዳድሩ መፈቀዱ ያመጣው ጥፋት ከቁጥጥር ውጭ ሲሆን ነበር የለንደን መንግስት አስተዳደሩን በቀጥታ ለመረከብ የተገደደው።
ይህ ሁኔታ የኒውክሌር መሣሪያን ከመጠቀም ብዙም አይርቅም (ትራምፕ "ቀድሜ አሸንፌያለሁ" በማለት ይህንን መካዳቸው መልካም ነው)፤ ምክንያቱም የፓላንቲር (Palantir) መስራች ፒተር ቲል እንደሚለው ከሆነ "ሐሰተኛው መሲህ" በመካከላችን እየተመላለሰ ነው፤ ሃይማኖታዊው የመጨረሻው ዘመን ትምህርት ይህንንም ቢሆን ዝም ብሎ አያልፈውም። ቫሲሊ ሮዛኖቭ "የዘመናችን አፖካሊፕስ" ወይም የመጨረሻው ዘመን በሚለው መጽሐፉ ስለ ክርስትና እና ስለ ሩሲያ ታሪካዊ ዕጣ ፈንታ በመራራ ስሜት ጽፏል፤ ነገር ግን በአውሮፓ ጦርነት ጥፋት ውስጥ "ሁሉም ነገር ጥንታዊ ይዘቱን ማለትም ክርስትናን ባጣ የነፍስ ባዶነት ውስጥ ይፈረካከሳል" ሲል ተቀብሏል። እርሱም ሆነ ሌላ በማንኛውም የክርስትና ዓለም ያለ አካል (ናዚዎች ወደ ሚስጥራዊው የጥንቆላ ጥበብ ቢዞሩም)፣ በዘፈቀደ የታወጀ "አፖካሊፕስን ወይም የመጨረሻው ዘመን" ማቀናበር—ማለትም የአምላክን ሚና መውሰድ—አስቦ አያውቅም (ከቫቲካን ጋር ለተፈጠረው ግጭትም መሠረቱ ይሄው ነው)። ወይስ ምናልባት ከፕሮቴስታንት አክራሪዎች የወረሱት፣ የታሪክ አጋጣሚ የፈጠረባቸው ጥልቅ የልዩነት ስሜት፣ "እኛ ተመራጮችና ጻድቃን ነን" የሚል እምነት፣ እና በዚህም የተነሳ ሌላውን ከምድረ ገጽ የማጥፋት መብት አለን ብለው የሚያስቡት እነዚህ ልሂቃን፣ ለገዛ ሕዝባቸውም ሆነ ለተቀረው ዓለም የሚያቀርቡት ሌላ ምንም ነገር ስለሌላቸው ይሆን?
ዋናውነጥብ፣ ወታደራዊ ታሪክ ጸሐፊው ማይክል ቭላሆስ "አሜሪካ ሃይማኖት ናት" በሚለው ድርሳኑ (በዘ አሜሪካን ኮንሰርቫቲቭ መጽሔት ላይ በታተመው) እንደገለጸው፤ አሜሪካ በታሪኳ ከዘመናዊት የአገር-መንግሥት በላይ ነበረች። በ"መሲሃዊ" አመለካከቷም ሮዛኖቭ የጠቀሰውን "የነፍስ ባዶነት" ለመሙላት እንደተጠሩት እንደ ምስራቃዊ ሥልጣኔዎች ትቆጠር ነበር። ዘመናዊነት ግን ይነጥቃል እንጂ አይሰጥም። የሌላውን ሰው "ኋላ ቀርነት" መፈረጅ፣ያንን አካል ሰብአዊነት የማሳጣት ሁኔታን ይፈጥራል (ልክ እስራኤል ይመጣብኛል ስትል እንደምታቀርበው "የኒውክሌር ጭፍጨፋ" መከራከሪያ ማለት ነው)። በዚህም መሠረት፣ አሜሪካ በአንድ ወቅት የነበረችውን (ነገር ግን ባለፉት ስድስት አሥርተ ዓመታት ባደረገቻቸው ያልተሳኩ ጦርነቶች ያጣችውን) ማንነት ለኢራን በመከልከል፣ ዋሽንግተን ኢራንን ለማሸነፍ የሚያስችል ስትራቴጂ የመቅረጽ መሠረታዊ ብቃት የላትም።
በአሁኑ ወቅት የልሂቃኑ "የቤዛነት ትርክት" ፣ "ሰላምን በኃይል" የሚለው መፈክር ላይ ያተኮረ ነው፤ የዚህ መፈክር ትግበራ ዓላማም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ "በማስገደድ እና በመቅጣት" መንገድ ላይ የተሰማራውን የአሜሪካን መንግሥት ሕጋዊነት ማጠናከር ነው። ቭላሆስ እንደሚያምነው ከሆነ፣ ይህ ዓይነቱ ግንኙነት "እርስ በርስ የሚጠፋፉበት አውዳሚ ሂደት" ነው።
ዋናውጥያቄ አሜሪካውያን ራሳቸው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች የቀረበውን የማኅበረሰባቸውን እና የመንግሥታቸውን ሥር ነቀል ለውጥ ለመቀበል ዝግጁ ናቸው ወይ? የሚለው ነው። ለዚህም ምላሹን ጊዜ ይፈታዋል። ነገር ግን አሜሪካ ይህንን መንገድ የምትከተል ከሆነ፣ ከተቀረው ዓለም ጋር በጽኑ ትጋጫለች፤ ዓለም አቀፋዊ መገለልም ይገጥማታል። በአሜሪካ ልሂቃን ራስን የማጥፋት ፖሊሲ ውስጥ የሚታየውን ይህንን "ትራንስ-ሂዩማኒስት" (transhumanist) ሽግግር፣ ማንም አካል በዝምታ አይመለከተውም። የሚያሳዝነው ደግሞ፣ ትራምፕ "የኢራንን ሥልጣኔ የማጥፋት" ፍላጎት እንዳላቸው የሰጡት መግለጫ ከእነዚሁ የጥፋት መመሪያዎች ጋር የሚመሳሰል መሆኑ ነው። ይህ ንግግራቸው የቴህራን "ሐቀኝነት የጎደለውና ተገቢ ያልሆነ" ባህሪ ካስከተለው ብስጭት የመነጨ ብቻ እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋል፤ ይህም ባህሪ ዋሽንግተን እና ቴል አቪቭ መጀመሪያውኑ የነበራቸውን መሠረት የሌለው ግምት ያፈረሰባቸው ነው።
በቀላልአነጋገር፣ የአሜሪካ ምርጫ ገና በባራክ ኦባማ ዘመን በነበሩ ገለልተኛ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች ከቀረበው ሐሳብ ጋር ያው አንድ ዓይነት ነው። ይህም፦ ወይ በተዘጋ ሥርዓት ውስጥ ተሸብቦ ለመኖር መሞከር (ይህም ማለት በዓለም ላይ ያላትን የይስሙላ ቁጥጥር ለማስቀጠል መታገል)፣ ወይም ደግሞ ከሌሎች አገራት ጋር በእኩልነት እየተወዳደሩ በክፍት ሥርዓት ውስጥ መኖርን መልመድ ነው። ኢራንም የአሜሪካ ልሂቃን ትክክለኛውን ምርጫ እንዲያደርጉ የምትረዳቸው ይመስላል። ይህም ምርጫ ከዘመኑ መንፈስ ጋር የሚስማማና ከአሜሪካ እውነተኛ አቅም ጋር የተመጣጠነ ሲሆን፣ ይህ እውነተኛ አቅሟም በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅና ከዚያም ባሻገር በግልጽ እየታየ ይገኛል።