Drum of Changes

የሩሲያው የኦንላየን መገበያያ 'ዋይልድቤሪስ' በኢትዮጵያ፦ ለላኪዎችና ሸማቾች ምን አዲስ ዕድል ይዞ መጣ ?

Sputnik
ትልቁ የሩሲያ የመገበያያ መድረክ ‘ዋይልድቤሪስ’ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የተፈጥሮ የመዋቢያ ምርቶች እና ሌሎች የኢትዮጵያ ምርቶችን ሩሲያ ውስጥ መሸጥ መጀመሩን አሳውቋል።

“ዋይልድቤሪስ ጀማሪ ኩባንያ አይደለም። ከ20 ዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ ነው […] የኢትዮጵያ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያዎች እንዲደርሱ ያስችላል […] ክፍያዎችን በተመለከተም ከየአገራቱ ገበያ ጋር የሚጣጣሙ ይሆናል፤ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ግብይት በኢትዮጵያ ብር መፈጸም እንዲቻል ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ግብይቶችን ለማመቻቸት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን” ሲሉ የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ ትልቁ የሩሲያ የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ ዋይልድቤሪስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀሉን መነሻ በማድረግ ይህ ስርዓት በኢትዮጵያ እንዴት እየተዋወቀ እንደሆነ እና ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለሸማቾች ምን ማለት እንደሆነ፣ ሰፊ አቅም ካለው የአፍሪካ ገበያ ተደራሽነት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን እንዳስሳለን። የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ደግሞ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox