'' የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለይ ከጎርጎሮሲያኑ 2000 ወዲህ ከፍተኛ ችግሮች እየገጠሙት ይገኛል — የተቋቋመበትን የዓለም አቀፍ ሰላምና ድኅንነትን የማስፈን ተግባር በተቋቋመበት ዓለማ አስጠብቆ እየሄደ ነው ለማለት አዳጋች ነው። ስለዚህ ባለብዘ ወገን ስርዓት እየተፈጠረ ባለበት ዓለም ተገዳዳሪ አየሆኑ የመጡ ሀገራትን ያካተተ፣ ድምፃቸውንም የሚያስተጋባ መሆን አለበት'' - ሲሉ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ ዓለም ከነጠላ የፖለቲካ ስርዓትና አስተዳደር ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተሸጋገረች ባለችበት በዚህ ወቅት የዓለም ሀገራትን በአንድ አቅፎ የያዘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጣይ እጣፈንታ ምን ሊመስል ይችላል የሚለውን ጉዳይ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ጋር ዳሰነዋል። በክፍል ሁለት በቅርብ ወደ ትግበራ የገባው የሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ ወይም ‘ስማርት ፖሊስ ስቴሽን ጉዳይ ኢንስፔክተር አንድነት ሲሳይ፤ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ኦፕሬሽን ዋና ክፍል ኃላፊ አጠቃላይ ቅኝት ያደርጉልናል፡፡
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox