Drum of Changes

ለዘላቂ ሰላም ወይስ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት? የኢራን-አሜሪካና እስራኤል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም እንቆቅልሽ

Sputnik

“ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በፈርጆቹ መጋቢት 7፣ 2026 በሆርሙዝ ሰርጥ የመጓጓ ነፃትን ለማስከበር የኃይል አማራጭን ለመውሰድ የጸጥታው ምክር ቤት ቀርቦ የነበረውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በሩሲያና ቻይና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ውድቅ መሆኑን እንመለከታለን። ይህ ሁኔታ አቅሙ እየተዳከመ ስለመጣው የምዕራቡ ዓለም ሁኔታ ምን ይነግረናል? የእዮብዘር ዘውዴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየታቸውን አጋርተዉናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox