"በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ላይ ባደረግነው ጥናት መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት ለቡና ልማት የምንጠቀምበት አካባቢ ወደ 60% የሚጠጋው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊጠፋ እንደሚችል ደርሰንበታል። አንዱ የመላመጃ መንገድ ደግሞ ቡናን በከፍተኛ ከፍታ ላይ ወደሚገኙ ቦታዎች ማዛወር ሲሆን፣ እነዚህ ከፍተኛ ቦታዎች ግን የደን ሽፋናቸውን ያጡ ናቸው። ስለዚህ የ'አረንጓዴ አሻራ' እና ሌሎች የደን ልማት ተነሳሽነቶች ደኖች እንዲያገግሙ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።" ሲሉ የአካባቢ እና የቡና ደን ፎረም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ታደሰ ወ/ማርያም (ዶ/ር) ስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በቅድሚያ የአካባቢ እና የቡና ደን ፎረም ዋና ዳይሬክተር ታደሰ ወልደማርያም (ዶ/ር) ጋር በመሆን፤ የኢትዮጵያን ልዩ የቡና ቅርስ እና ያለውን ሥነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታ እንመረምራለን፤ በማስከተልም በኢቲ ሀይላንድ ፍሎራ የእርሻ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት ከእመቤት ተስፋዬ ጋር በመሆን፤ በኢትዮጵያ እያደገ ያለውን የሆርቲካልቸር ዘርፍ እንቃኛለን፤ በመጨረሻም ከራሄል አዊንሱ አላቢላ (ጋና) እና ታቢታ ጆሴፍ (ኬንያ) ጋር በመሆን፤ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት እና የዛሬው ወጣቶች ይበልጥ ሉዓላዊና የተባበረ የወደፊት ጊዜን እንዴት እየቀረጹ እንደሆነ እንወያያለን።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox