Continental Drift

የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች

Sputnik
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የዓለምን የኢነርጂ ፍሰት እና ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፍ እየቀየረ ነው ። በተለይም በሆርሙዝ የባህር በር ላይ የሚፈጠር አለመረጋጋት በአፍሪካ የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው ።
"አፍሪካ አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር ተጋላጭነቷን እና ጥገኝነቷን ለመቀነስ መሞከር ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ በጣም ጥሩ ምሳሌ ናት። ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በአንድ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምንጮቿን በማባዛት ረገድ የተሳካ ስራ ሰርታለች።" ሲሉ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ባለሙያ ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እና በአጠቃላይ በደቡባዊው የዓለም ክፍል ላይ የሚያሳድረውን ዘለቄታዊ ተጽዕኖ በሶስት የተለያዩ አቅጣጫዎች እንቃኛለን ። ለዚህም ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ፣ በዱባይ ይኖር ከነበረው ተማሪ አናኦል ሚካኤል እና ከስትራቴጂክ ተንታኙ ሚካኤል ገዛኸኝ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox