"አሜሪካ የገዛ ጥቅሟን ለማስከበር ሲባል ጦርነቶችን ከመደገፍ ወደኋላ የማትል ሀገር ናት። ሳዳም ሁሴንን መጠቀም ሲፈልጉ ደግፈውታል። ነገር ግን አንዴ ተልዕኮአቸውን ከፈጸሙብህ በኋላ ወይም የእነሱን ፖሊሲ መቃወም ስትጀምር፣ ለእነሱ ዓላማ ከእንግዲህ ስለማታገለግል ሊያጠፉህ ይነሳሉ። ኢራቅ ላይ የሆነው ይህ ነው፡፡ የወረራው ምክንያት 'የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎችን መፈለግ' እንደነበር ቢነገርም፣ ቶኒ ብሌየር እና ጆርጅ ቡሽ እንደዋሹ አሁን ላይ ሁላችንም እናውቃለን፤ ነገር ግን በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍትህ ሥርዓት ፊት ማነው ተጠያቂ ሊያደርጋቸው የሚችለው? ተጠያቂ ሊሆኑም አይችሉም። ይህም የሚያሳየው እነዚህ [የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት] ተቋማት የተመሰረቱት የአውሮፓ ኃያላን ሌሎችን ለመቅጣት እንጂ ራሳቸውን ለመጠየቅ እንዳልሆነ ነው።" ሲሉ በ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ትምህርት ክፍል ከፍተኛ መምህርና ተመራማሪ ለሄሳ ሞሎይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እየተባባሰ የመጣው የኢራን-እስራኤል-አሜሪካ ግጭት ለደቡባዊው የዓለም ክፍል ምን ትርጉም አለው? ይህ ቀውስ ቀጠናዊ ክስተት ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ያለው ትልቅ መለወጫ ነጥብ ነው። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ትምህርት ክፍል ከፍተኛ መምህርና ተመራማሪ ከሆኑት ከ ለሄሳ ሞሎይ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ከዜናዎቹ በስተጀርባ ያለውን ጥልቅ ታሪክ፣ ፖለቲካ እና በደቡባዊ ዓለም ላይ የሚያሳደረውን ተጽዕኖ እንዳስሳለን።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox