“ከዚህ ቀደም ምዕራባውያን በአካል መጥተው የወረሩን ጊዜያት ነበሩ። የአፍሪካን ሕዝብ በቅኝ ገዝተዋል። ዛሬ ግን ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል። አሁን ደግሞ በመረጃ ቋቶቻቸው አማካኝነት ሊገዙን እየሞከሩ ነው። የማይወክሉንን ነገሮች ሁሉ እየሰበሰቡ ‘የእናንተ ተሞክሮ ይህ ነው’ ይሉናል። ነገር ግን ያ እኛን አይገልጸንም። ለዚህ ነው አፍሪካውያን የራሳችን የሆነ ‘የመረጃ ስብስብ’ እና የራሳችን የሆነ የቋንቋ ማቀነባበሪያ ዘዴ (Language processing) ሊኖረን የሚገባው።” ሲሉ በርቀት እና ኢ-ለርኒንግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አደራጀው ምህረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስለ አፍሪካ ምን ማወቅ እንዳለበት የሚወስነው ማነው? አፍሪካስ የራሷን ታሪክ በየትኛው ቋንቋ ትናገራለች? በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዶ/ር አደራጀው ምህረት ጋር ስለ "አልጎሪዝም የበላይነት" እንወያያለን። እንዲሁም በኢትዮጵያ የኩባ ከአምባሳደር ሜይሊን ሱዋሬዝ አልቫሬዝ እና ሌሎችም ጋር በመሆን ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀንን እናከብራለን፤ በኮድ እና በባህል ውስጥ ያለውን "የትርክት ሉዓላዊነት" ትግልም በጥልቀት እንመረምራለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox