Drum of Changes

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ፣ የአፍሪካ አገራትን እንዴት ሊጎዳ ይችላል ?

Sputnik
የመካከለኛው ምስራቅ ቀዉስ የነዳጅ ዋጋን ብሎም የዋጋ ግሽበትን እያባባሰ ባለብት ሁኔታ አፍሪካ ቆማ መመልከት አትችልም። አማራጭ የኃይል አቅርቦት ላይ ማተኮር፣ ቀጣናዊ ትስስርን ማፋጠን ግድ ይላታል።
“ለአፍሪካ ይህ በጣም መጥፎ ዜና ነው። የነዳጅ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አብዛኞቹ አገራት እንዲህ ዓይነቱን ጫና ለቋቋም እጅጉን ይቸገራሉ። [...] ስለዚህ የአፍሪካ አገራት ስለ አማራጭ የኃይል ምንጮች የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው።እንደሚታወቀው አፍሪካ ብዙ አማራጮች አሏት”ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን የጦር ዘመቻ ተከትሎ በአፍሪካ ላይ የሚመጣውን ሁለንትናዊ ጫና እና መፍትሄዎቹን በተመለከተ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግርናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ መጋቢት 17-18 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አራተኛውን “በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረምን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ቆይታ ታደምጣላችሁ።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerAfripods Spotify Pocket Casts Podcast Addict CastBox