“አፍሪካውያን የራሳቸውን ታሪክ በራሳቸው መንገድ እና አተራረክ ዘዬ ማቅረብ አለባቸው የሚል ትልቅ የፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ አለ። […] ያ ትግል ረጅም ዓመት ሄዷል፣ ግን ያን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም። ውጤታማ እንዳይሆን ያደረገው ትልቁ ምክንያት የመረጃ ክፍተት ነው። መረጃ ደግሞ ኃይል መሆኑን የምታውቀው ቢያንስ የራስህ ባይሆን እንኳን አንተ የምትቆጣጠረው ሚዲያ ወይም በአንተ መጫወቻ ሜዳ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ነው።” ሲል በስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ አዘጋጅ እና አቅራቢ ዐብይ ሀብታሙ ተናግሯል።
በዚህኛው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍቶ ስርጭት የጀመረበትን 1ኛ ዓመት አስመልክቶ የመጀመሪያው ዓመት የሥራ መልኮቻችንን ቅኝት አድርገናል። ለዚህም በኢትዮጵያ የስፑትኒክ አፍሪካ አዘጋጅ እና አቅራቢ ከዐብይ ሀብታሙ እና ዘላለም ደምሴ ጋር ቆይታ አድርገናል።
“እንደ ስፑትኒክ ያሉ ትልቅ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን፣ ተሰሚነት ያላቸው መገናኛ ብዙሃን በቋንቋችንም፣ በእንግሊዝኛውም ደግሞ ስራ መጀመራቸው አፍሪካውያን ስለ አፍሪካ፣ ስለ ራሳችን ያለንን ግምት ከመቀየር አንጻር በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።” ሲል በስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮአዘጋጅ እና አቅራቢ የሆነው ዘላለም ደምሴ አክሏል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox