Continental Drift

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል:- የሉዓላዊነት መሠረትና የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አቀጣጣይ

Sputnik
የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የተመዘገበው የዓድዋ ድል ጣሊያንን በጦር ሜዳ የማሸነፍ ጉዳይ ብቻ አይደለም።አፍሪካውያን በራሳቸው መደራጀት እና ማሸነፍ እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት የታሪክ ምዕራፍ ጭምር እንጂ። ዛሬም ግን የሉዓላዊነት ጥያቈ መልኩ ብዙ ሆኖ እያየነው ነው።
"አፍሪካ ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳትጠይቅ በጠንካራ አቋም ወደ ድርድር ጠረጴዛው መምጣት አለባት። እነዚህን ሐሳቦች ስላስተዋወቅን ብቻ ‘ባህላዊ’ ጉዳዮች ሊባሉ አይገባም፤ ምክንያቱም ይህ ማንነታችን በመሆኑ ወሳኝ ነው።[...]‘ጭራው ውሻውን እንዲያወዛውዝ’ መፍቀድ የለብንም።" ሲሉ ፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ለስፑቲክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የዓድዋን ድል ከወቅታዊው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል ጋር በማገናኘት ከፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox