የ2026ቱ 'ዊንተር ኦሊምፒክ' ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 22፣ 2026 (እ.ኤ.አ) በሰሜን ጣሊያን ሚላን እና ኮርቲና ዲአምፔዞ በተባሉ ቦታዎች እየተካሄደ ነው። ይህ ሁነትም ከ20 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በበረዶ ሸርተቴ የወከለውን አትሌት ያስታወሰናል፤ ሮቤል ተክለማርያም።
"ማንኛውም ስፖርተኛ ሊያገኘው የሚችለው ትልቁ ክብር አገሩን መወከል ነው። ባንዲራ ይዞ መሄድ፣ በታላለቅ መድረኮች ላይ ሀገርን ወክሎ ወደ ውድድር ቦታዎች መግባት በጣም የተለየ ስሜት አለው። የማይረሳ ተሞክሮ ነው … በክረምት ስፖርቶች ለመወዳደር ለሚፈልጉ ሌሎች የአፍሪካ አትሌቶች ሁሉ፣ መልእክቴ ቀላል ነው አለመታከት መቀጠል!" ሲል በክረምት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከ20 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በበረዶ ሸርተቴ የወከለው ሮቤል ተክለማርያም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጥንቅራችን ኢትዮጵያን በበረዶ ሸርተቴ በ 'ዊንተር ኦሊምፒክ' በመወከል እ.ኤ.አ. 2006 በጣልያን እንዲም 2010 በካናዳ ቭነኮቨር የተወዳደረውን ብቸኛ አትሌት ሮቤል ተክለማርያም እንግዳችን አድርገነዋል። ከሮቤል ጋር ስለትጋት፣ በሀገር መመካትን ማንነትን የተመለከቱ ጉደዮችን እናነሳለን። በሁለተኛው ክፍል ዝግጅታችንም በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሳታፊዎችን በማነጋገር ወቅታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ቆይታውን ያደርጋል። ለዚህም በአዲስ አበባ የዩኔስኮ ጽህፈት ቤት ባልደረባ የሆኑትን አሊ ዳዎን እና የጋና መንግስት ልዑካን ቡድን ባልደረባ የሆኑትን ኤክዎው ስፒዎ ጋርብራህ (ዶ/ር) አነጋግረናል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox