እንደ ፓን አፍሪካ የክፍያ ስርዓት ያሉ ተነሳሽነቶች ዶላር ላይ የቀጠለውን ጥገኝነት የመቀነሳቸው ጉዳይ ከንድፈ ሀሳባዊ ውይይት ያለፈና ተግባራዊ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው።
“የጋራ የክፍያ ስርዓት ጉዳይ እና የጋራ መገበያያ ገንዘብ አለመኖር በተለይም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙሪያ የሚጠበቁ እድገቶችን ከሚያደናቅፉ ማነቆዎች ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። ስለዚህ እንደ የፓን አፍሪካ የክፍያ ስርዓት ያሉ ስርዓቶች በአፍሪካ አገሮች መካከል ያለውን ንግድ እና ግብይቶችን ለማቃለል ሊረዱ ይችላሉ።" ሲሉ የንግድ እና ዘርፋ ማህበራት ዋና ፀሐፊ ቀነኒሳ ለሚ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ በአዲስ አበባ የተካሄደውን 15ኛውን የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት መነሻ አድርገን አህጉር አቀፍ የክፍያ ስረዓቶችን ቀዳሚነት እንመለከታለን። ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፋ ማህበራት ዋና ፀሐፊን ቀነኒሳ ለሚ (ዶ/ር) እንግዳ አድርገናል። ቀጥለን የሶማሊያ እና ጅቡቲ ፕሬዝደንቶች በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት መነሻ በማድረግ ከሀገራቱ ሁለንተናዊ ግንኙነት አንፃር የሚኖረዉን አንድምታ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ሚፍታህ መሐመድ ጋር እንዳስሳለን።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts –Deezer – Afripods –Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox